
አድማጮቻችን ባሳለፍነው ሳምንት በመዲናችን በአዲስ አበባከተማ የእንግሊዙ አርሰናል ክለብ የ2025/2026 የፕሪሚየር ሊግአሸናፊ መሆኑን ተከትሎ ደጋፊዎቹ ደመቅ ያለ የደስታኮንሰርትና የተለያዩ ዝግጅቶችን ማድረጋቸው ይታወሳል።የክለቡ የቀድሞ ኮከብ ኢማኑኤል ኢቦዬና የAFTV ሚዲያአባላትም በነዚህ ዝግጅቶች ላይ ታድመው ነበር።
ታዲያ ይህንን ወቅታዊ አጋጣሚ በመጠቀም በማህበራዊሚዲያ ላይ የተሰራጨ አንድ መነጋገሪያ ምስል ሳትመለከቱአልቀራችሁም።
Mr Teddy የተባለና ከ58 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክገጽ እንዲሁም ኢማኑኤል ኢቦዬና የAFTV ቡድንበቤተመንግስት ሙዚየም ውስጥ “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይናለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ትልቅ ባነር ይዘውቆመዋል የሚል ምስል አጋርቶ ተመልክተናል።
ልጥፎቹ በድምሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የላይክ የኮመንትናየማጋራት ግብረ-መልስ በማግኘት ሰዎችን ሲያደናግሩቆይተዋል።ለመሆኑ የአርሰናል ደጋፊዎችና እንግዶቹ በእርግጥይህንን የፖለቲካ መልዕክት የያዘ ባነር ይዘው ተነስተዋል?
ትርታ ቼክ ጉዳዩን በዲጂታል መሳሪያዎችና በጥልቅ ምልከታአጣርቶታል። ምስሉን ይዘቱ የተቀየሩ ፎቶዎችን ለመመርመርወደሚረዳው FotoForensics ድረ-ገጽ በማስገባት ምርመራያደረግን ሲሆን ። በውጤቱም “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይናለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚለው ጽሑፍየሰፈረበት ባነር ሙሉ በሙሉ በኋላ ላይ በቅንብር የተጨመረመሆኑን አረጋግጠናል።
በተጨማሪም illuminarty.ai በተባለው የዲጂታል መመርመሪያመሳሪያ ባደረግነው ማጣራት ባነሩ 88% በሰው-ሰራሽአስተውሎት (AI) የተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃአግኝተናል
በመሆኑም የአርሰናል ደጋፊዎችንና እንግዶቹን ምስልበመጠቀም “ለዶ/ር ዐቢይ ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ባነርይዘዋል ተብሎ የተሰራጨው ፎቶ… በAI የተቀነባበረና ፍጹምሐሰተኛ መሆኑን ትርታ ቼክ ያረጋግጣል።
አድማጮቻችን፤ በተለይ ወቅታዊና ትኩረት የሚስቡየስፖርትም ሆነ የፖለቲካ ክስተቶችን ተገን በማድረግ፣ እውነተኛምስሎች ላይ የፈጠራ ይዘቶችን በመጨመር ሰዎችን ለማሳሳትየሚጋሩ መረጃዎች ስለሚበራከቱ ማንኛውንም መረጃከማመናችንና መልሰን ለሌሎች ከመጋራታችን በፊትተገቢውን ማጣራት እንድናደርግ ትርታ ቼክ ያሳስባል።
ቤተሰቡን ይቀላቀሉ:
🌕Facebook: Tirita 97.6 FM
🌕YouTube: Tirita Radio
🌕Instagram: tiritafm
🌕LinkedIn: Tirita FM 97.6