ጃል ዳንኤል ጃርሶ በዝረራ አሸንፏል” በሚል የተሰራጨው የሀሰት ምስል

ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ በተለይም “Sidama Times” በተሰኘውና ከ7 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገፅ ላይ አንድ አነጋጋሪ መረጃ ከምስል ጋር ተሰራጭቶ ተመልክተናል።

ይህ ልጥፍ ሰበር መረጃ በሚል የ22 ማፍያ ቡድን መሪ ጃል ዳንኤል ጃርሶ በዝረራ አሸንፏል! ኦሮሞ መሆን ቀርቶ ኦሮሞ ነኝ ብቻ ካልክ አስፈሪ ሆነህ ትኖራለህ!” የሚል ስሜት ቀስቃሽ ቃላትን የተጠቀመ ፅሁፍ ያካተተ ሲሆን፤ በምስሉም ላይ የፖሊስ ልብስ የለበሱ የፀጥታ አካላት መሬት ላይ ተደፍተው አንድ ባህላዊ ልብስ የለበሱ ግለሰብ ደግሞ በመሃል ሲያልፉ ያሳያል።

https://www.facebook.com/share/1Dymhi2nJf/

ይህ መረጃ ትርታ ቼክ ጉዳዩን አጠናክሮ እስካደረሰበት ሰዓት ድረስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ150 በላይ Likes እና ከ50 በላይ Shares በማግኘት በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሲዘዋወር ቆይቷል።

ትርታ ቼክ ከመረጃው ጋር ተያይዞ የተሰራጨውን ይህንን ምስል በጥንቃቄ የተመለከተ ሲሆን የምስሉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥም “AI or Not” የተሰኘውን ዘመናዊ የዲጂታል ምስል መመርመሪያ መሳሪያ ተጠቅሟል።

በተደረገው የቴክኖሎጂ ማጣራት መሰረት ይህ ምስል በተጨባጭ መሬት ላይ የተከሰተን እውነተኛ ክስተት የሚያሳይ ሳይሆን፣ዠ ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም AI (Artificial Intelligence) የተቀነባበረ እና የተፈበረከ መሆኑን አረጋግጠናል። ምስሉን በጥንቃቄ ለተመለከተ ሰውም ቢሆን በምስሉ ላይ ያሉ የተወሰኑ አካላት ተፈጥሯዊ አለመሆንና በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ የተሰሩ መሆናቸውን በቀላሉ መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም ምስሉ በፖለቲካዊ እና በብሔር ስሜት ዙሪያ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ሆን ተብሎ በቴክኖሎጂ የተፈበረከ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ትርታ ቼክ ያረጋግጣል።

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!