በትግራይ ክልል የድሮን ቅኝት ተደረገ በሚል የተሰራጨው ምስል እውነታ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ዲጂታል ኢትዮጵያበተሰኘና ከ36 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት ገፅ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል ቁልፍ ቦታዎች ላይ የድሮን ቅኝት ማድረጉን የሚገልጽ ሰበር ዜናበምስል ታጅቦ ሲሰራጭ ተመልክተናል። ልጥፉ የአየር ኃይሉ የህወሓትና የሻዕብያ የጦር ካምፖችንና መደበቂያዎችን መቃኘቱን የሚገልጽ ሲሆን፣ እስካሁን ከ1,100 በላይ ‘Like’ እና ከ50 በላይ ‘Share’ ተደርጓል።

ትርታ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ምስሉን በዲጂታል የማጣሪያ ዘዴዎች የመረመረ ሲሆን በጎግል ሌንስ ባደረግነው የገጽታ ፍለጋ ማጣራት፣ ምስሉ አሁን በትግራይ ክልል የተነሳ ሳይሆን በፈረንጆቹ May 9, 2025 caspianpost.com በተባለ ዓለም አቀፍ የዜና ድረገጽ ላይ የወጣ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። በምስሉ ላይ የሚታየው ድሮን የቱርክ ምርት የሆነው Bayraktar Akıncı ሲሆን፣ በሁለተኛው ምስል ላይ በድሮኑ ጭራ ላይ የቱርክ ባንዲራ ምልክት በግልጽ ይታያል። ይህም ምስሉ ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ወቅታዊ እንቅስቃሴ ጋር የማይገናኝና ከሌላ የውጭ ሀገር ምንጭ የተወሰደ መሆኑን ያሳያል።

በትግራይ ክልል የድሮን ቅኝት ተደረገ በሚል በዲጂታል ኢትዮጵያገፅ የተሰራጨው ምስል የቆየና ከሌላ ዓለም አቀፍ ድረገጽ የተወሰደ በመሆኑ፣ የቀረበው መረጃ መሠረተ ቢስ መሆኑን ትርታ ቼክ አረጋግጧል ።

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!