አንድ ወታደር ዜጎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲመርጡ እያስገደደ ነው በሚል በAI የተሰራጨው የቪዲዮ ማጭበርበሪያ

አድማጮች ከዚ ሀሰተኛ መረጃ ጋር በተያያዘ ዲጂታል ማጭበርበርን በመጠቀም ህዝብን ለማስፈራራት የታለመ አንድ አስደንጋጭ ቪዲዮ በፌስቡክ ላይ ተለቆ ተመልክተናል ቪዲዮው አንድ የፀጥታ ሀይል ወታደር ዜጎችን ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲመርጡ በሃይል ሲያስገድድ ያሳያል

 

 

ምንም እንኳን ቪዲዮው የቴክኖሎጂ ማጭበርበሩን በቀላሉ የሚያጋልጡ ግልጽ የሆኑ የቴክኒክ ጉድለቶች ያሉበት ቢሆንም፣ በቪዲዮው ስር ያሉትን የተለያዩ ሰዎች አስተያየቶች ግን በርካታ ተመልካቾች በነገሩ ተሸውደው በከፍተኛ ስጋትና ድንጋጤ ውስጥ መውደቃቸውን ተመልክተናል ።

 

 

ትርታ ቼክ የቪዲዮውን ትክክለኛነት እና ምንጭ ለማረጋገጥ የቪዲዮ ማጣሪያ ዲጂታል መሳሪያዎችን ተጠቅሟል። በምርመራው መሰረት ይህ ቪዲዮ በተጨባጭ መሬት ላይ የተከሰተን ክስተት የሚያሳይ ሳይሆን፣ ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም AI ቴክኖሎጂ ተዘጋጅቶ የቀረበ የፈጠራ ድራማ መሆኑን አረጋግጠናል።በመሆኑም ወታደሩ ህዝቡን ለምርጫ እያስገደደ ነው የተባለው ቪዲዮ ህዝብን ለማስፈራራት ሆን ተብሎ AI የተሰራጨ የሀሰት መረጃ መሆኑን ትርታ ቼክ ያረጋግጣል።

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!