በቤንሳ ወረዳ የመራጭ ካርዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ በሚል የተሰራጨው የድሮ ምስል

ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ላይ በርካታ የመራጮች ምዝገባ ካርድ በፌስታል ተሞልቶ የሚያሳይ ምስል በማያያዝ፣ መጠነ ሰፊ የምርጫ ማጭበርበር እየተካሄደ ነው የሚል መረጃ በስፋት ሲሰራጭ ተመልክተናል ።በምርጫ ህግ መሰረት አንድ የመራጭ ካርድ ለአንድ ዜጋ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ ካርዶችን በጅምላ አከማችቶ መገኘት ሙሉ በሙሉ ህገወጥ ነው ይህንን የጉዳዩን ስሜት ቀስቃሽነት በመጠቀም፣ ታዋቂው ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ (Jawar Mohammed) ምስሉን በፌስቡክ ገጹ ላይ አጋርቷል

 

ይህ በሲዳማ ክልል በቤንሳ ምርጫ ክልል ውስጥ የሚገኝ የአንድ ወረዳ ካቢኔ አባል ቤት ውስጥ የተገኘ የመራጭ ካርድ ነው ምስሉን አያይዞ በማህበራዊ ሚድያ ሲዘዋወር ቆይቷል ከእርሱ ልጥፍ በኋላ መረጃው በተለያዩ አውታሮች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የተሰራጨ ሲሆን

አንዳንድ ሌሎች አካውንቶች ደግሞ ምስሉን ከአማራ ክልል (አዊ ዞን) ጋር በማያያዝ አጋርተውታል ፖለቲከኛው በኋላ ላይ ልጥፉን ከገጹ ላይ ቢያጠፋውም ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ግን የአካባቢው ባለስልጣናት ገዥው ፓርቲን ለማሸነፍ ካርዶችን በምስጢር እያከማቹ ነው በሚል ምስሉን አሁንም በስፋት እያሰራጩት ይገኛሉ

 

ትርታ ቼክ ምስሉን እና የተጋራውኝ ፅሁፍ ተመልክቶ ይፋዊ ሰነዶችንና የቆዩ መዝገቦችን በማጣራት ባደረገው ምርመራ ምስሉ 2013 . የተነሳ የቆየ ምስል መሆኑን አረጋግጠናል ምስሉ አሁን ከሚነገረው የፖለቲካ አውድም ሆነ ወቅታዊ ክስተቶች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ።በመሆኑም የቆየ ምስልን ለአሁኑ ምርጫ ማጭበርበሪያ ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ ፍጹም የተሳሳተና ህዝብን ለማደናገር ሆን ተብሎ የተሰራጨ በመሆኑ ትርታ ቼክ ሀሰተኛ ሲል በይኖታል።

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!