ከመንግሥት ሰራተኛ ግብር 15% ተቀነሰ በሚል የተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ

ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች በተለይም በፌስቡክ ላይ በሚንቀሳቀሱ ትላልቅ ገጾች ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ከመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ግብር ላይ የ15 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ የሚል መረጃ በስፋት ሲዘዋወር ሰዎችን ሲያነጋግር እና ሲቀባበሉት ተመልክተዋል?

ይህ መረጃ በተለይ ሀብን ሀዲያ Ethiopia” በተሰኘውና ከ23 ሺህ በላይ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፅ ላይ ተጋርቶ ትርታ ቼክ መረጃውን እስካጠናከረበት ሰዓት ድረስ ከ900 በላይ መውደዶች Likes,እና ከ139 በላይ ማጋራቶች Shares,አግኝቶ ተመልክተናል። በርካታ የመንግስት ሰራተኞችም ጉዳዩ እውነት መስሏቸው በተስፋ ሲወያዩበት መስተዋሉ የነገሩን አሳሳቢነት ይጨምረዋል።

https://www.facebook.com/100072428705381/posts/975732618184353/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ትርታ ቼክ የዚህን መረጃ እውነተኝነት ለማረጋገጥ ይፋዊ ሰነዶችን መፈተሽ እና ተቋማዊ ምንጮችን ማነጋገርን ጨምሮ የተለያዩ የማጣሪያ መንገዶችን ተጠቅሟል።

በዚህም መሰረት የገንዘብ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ በራሱ ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ላይ የሰጠውን ምላሽ ተመልክተናል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ፦ የተቋሙን ስምና መለያ በመጠቀም ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ እና የደመወዝ መጠን መሰረት ያደረገ ማሻሻያተብሎ በደብዳቤ መልክ ጭምር እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ፍጹም ሀሰተኛ እና የተፈበረከ መሆኑን አስታውቋል።

https://www.facebook.com/100064767786633/posts/1427912679377645/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

በመሆኑም ከመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ግብር ላይ የ15% ቅናሽ ተደረገ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ትርታ ቼክ አረጋግጧል።

 

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!