የሀይማኖት አባትን ምስል በመጠቀም የተሰራጨው የተጭበረበረ የቅስቀሳ መረጃ

ሌላው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተዘዋወረ የሚገኘው መረጃ፣ አንድ ታዋቂ የሀይማኖት አባት ለገዥው ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው የሚል ስሜት ቀስቃሽ ምስል ነው

በተለቀቀውና በተቀነባበረው ምስል ላይ የኢፌድሪ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እውቅ የሀይማኖት አባት የሆኑት መልአከ ኃይል አባ አፈወርቅ ዮሐንስ፣ የብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ምልክት የሆነውን የስንዴ እሸት ይዘው ይታያሉ

 

ምስሉ በርካታ ጥርጣሬዎችን የሚያስነሳ ቢሆንም፣ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና ታዋቂ አክቲቪስቶች እንደ እውነተኛ መረጃ አድርገው በስፋት አጋርተውታል

ትርታ ቼክ የምስሉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ዲጂታል መመርመሪያዎችን ተጠቅሟል። በማጣራቱም መሰረት፣ ምስሉ ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም AI ቴክኖሎጂ አማካኝነት የተፈበረከ መሆኑ ተረጋግጧል የሀይማኖት አባቱ ትክክለኛ ፎቶግራፍ ላይ የተያዘውን ባህላዊ የክርስትና እጅ መስቀል በዲጂታል መንገድ በመቀየር፣ በምትኩ የፖለቲካ ፓርቲውን ምልክትስንዴውን በማስገባት የተሰራ የማጭበርበሪያ ስራ ነው

በመሆኑም የሀይማኖት አባቱ ለፖለቲካ ፓርቲ እየቀሰቀሱ ነው ተብሎ የተሰራጨው ምስል በAI የተፈበረከ የሀሰት መረጃ መሆኑን ትርታ ቼክ አረጋግጧል።

 

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!