በመቄት ወረዳ የሃይማኖት አባት ላይ ግፍ ተፈጸመ በሚል የተሰራጨው የምስል እውነት

አድማጮች በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በፌስቡክ ላይ ወጣቱ አማራ በተባለና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት ገፅ ላይ፣ በመቄት ወረዳ በአንድ የቤተክርስቲያን አባት ላይ በሠራዊቱ የግፍ እርምጃ ተፈፅሟል የሚል መረጃ ከምስል ጋር ተሰራጭቶ ተመልክተናል።

ይህ ልጥፍ የኦሮሙማ ብልፅግና ሥርዓት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት የሃይማኖት አባቶችን ኢላማ አድርጓልበሚል መሪ ቃል የቀረበ ሲሆን፣ በመቄት ወረዳ የሚገኙ አንድ ወፍጮ የሚያንቀሳቅሱ አባት ለፋኖ መረጃ ትሰጣለህ ትመግባለህ በሚል ሰበብ ታስረው እንግልት እንደደረሰባቸው ይገልጻል። ዜናውን ወደናንተ እስካደረስንበት ሰዓት ድረስ ይህ መረጃ ከ300 በላይ Like እና ከ140 በላይ Share ተደርጓል።

ትርታ ቼክ የመረጃውን እውነተኝነት ለማረጋገጥ በልጥፉ ላይ ጥቅም ላይ የዋለውን ምስል በዲጂታል ማጣሪያዎች የመረመረ ሲሆን፣ ምስሉን በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚሰሩ ምስሎችን በሚለየው AI or Not በተባለ የዲጂታል መሳሪያ ሲያጣራ ምስሉ በ AI የተቀነባበረ እንጂ እውነተኛ ክስተትን የሚያሳይ አለመሆኑ ተረጋግጧል።

በምስሉ ላይ የሚታዩት የገመድ አሰራር ሁኔታዎች፣ የሰውየው የሰውነት አቀማመጥ እና በአካባቢው ያሉ ጥላዎች ከእውነተኛ ፎቶግራፍ ይልቅ በቴክኖሎጂ የተፈጠሩ መሆናቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች ይታዩበታል።

በመሆኑም መረጃው የተሳሳተ እና በቴክኖሎጂ የተፈበረከ ምስልን በመጠቀም የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ የታለመ መሆኑን ተመልክተናል። በአክሱምም ይሁን በመቄት ወረዳ የሃይማኖት አባቶች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል በሚል በምስል የታጀቡት እነዚህ መረጃዎች መሠረተ ቢስ መሆናቸውን ትርታ ቼክ አረጋግጧል።

ትርታ ቼክ መረጃውን ሀሰተኛ ሲል በይኖታል።

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!