በሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ሞት ተፈርዶባቸዋል በሚል የተሰራጨው ምስልእውነታ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም ስቴሊን ገብረስላሴበተባለና ከ350 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገፅ ላይ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለሞት ፍርድ መዳረጋቸውን የሚገልጽ አሳሳች መረጃ በስፋት ሲሰራጭ ተመልክተናል። ልጥፉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የሳዑዲ መንግስት ምህረት እንዲያደርግላቸውና ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው የሚማጸን ሲሆን በምስሉ ላይም በርካታ ኢትዮጵያውያን በካቴና ታስረው በፖሊስ ታጅበው ሲሄዱ ያሳያል።

ይህ መረጃ እስካሁን ድረስ ከ2,500 በላይ Like እና ከ650 በላይ Share የተደረገ ሲሆን ብዙዎችን ያስደነገጠና የተሳሳተ ግንዛቤ የፈጠረ ሆኗል።

ትርታ ቼክ የመረጃውን እውነተኝነትና የምስሉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ምርመራ ያደረገ ሲሆን

በልጥፉ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ምስል በ AI የተቀነባበረ መሆኑን ለመለየት AI or Not በተባለ የዲጂታል መሳሪያ ምርመራ ተደርጓል። በምርመራው ውጤት መሰረት ምስሉ 100% በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረከ እንጂ በእውነተኛ ካሜራ የተቀረጸ አለመሆኑ ተረጋግጧል።

ምስሉን ያለ ምንም አይነት መሳሪያ በእይታ ብቻም ስንመለከተው በምስሉ ላይ የሚታዩት የፖሊስ ልብሶችና በላያቸው ላይ ያሉ ፅሁፎች ከሳዑዲ አረቢያ እውነተኛ የፖሊስ ዩኒፎርም ጋር የማይገጥሙና በዝርዝር ሲታዩ የማይነበቡ ናቸው።

ካቴና የታሰሩት ሰዎች የፊት ገጽታ እና የሰውነት ክፍሎች በተለይም እጆቻቸውና ጣቶቻቸው ላይ የሚታዩ ቅርጾች በ AI ምስሎች ላይ የሚታዩ የተለመዱ የተዛቡ ቅርጾች ናቸው። አልፎም በምስሉ ጀርባ የሚታዩት ህንጻዎችና የንግድ ምልክቶች ላይ ያሉት የአረብኛ ፅሁፎች ትርጉም የማይሰጡና የተደበላለቁ ናቸው።

ምንም እንኳን በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ እንግልቶችና እስራቶች እንደሚገጥሟቸው የሚታወቅ ቢሆንም አሁን የተሰራጨውና ኢትዮጵያውያን ለሞት ተፈርደው እየተወሰዱ እንደሆነ የሚያሳየው ምስል ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተቀነባበረ ነው። እንዲህ ያሉ መረጃዎች የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስና የተከታዮችን ቁጥር ለመጨመር ታስበው የሚሰሩ በመሆናቸው፣ ህብረተሰቡ መረጃዎችን ሳያጣራ እንዳያሰራጭ እናሳስባለን።

በመሆኑም ስቴሊን ገብረስላሴ በተባለው ገፅ የቀረበው መረጃና ምስል ሀሰተኛ መሆኑን ትርታ ቼክ አረጋግጧል።

በተጨማሪም

ሌሎች እውነታዎችን ያጥራናቸው መረጃዎች

Contact Us Now!

Do you have any Tikoma NEWS?

Share it with us NOW!

Are you looking to Advertize on Tirita FM?

Contact Us Now!

Contact Us Now!